Our Storyየእኛ ታሪክ

About Mental Abacus Academy

ስለ ሜንታል አባከስ አካዳሚ

Learn about our history, our educational mission, and the passionate trainers behind our students' success.

ስለ ታሪካችን፣ ስለ ትምህርታዊ ተልዕኳችን እና ለተማሪዎቻችን ስኬት በስተጀርባ ስላሉት ቀናተኛ አሰልጣኞች ይወቁ።

Who We Are
ማን ነን

Nurturing young minds through mental calculation

በአእምሮ ስሌት ወጣት አእምሮዎችን ማሳደግ

Mental Abacus Academy was founded with a singular vision: to unlock the latent cognitive potential of every child in Ethiopia. By blending time-tested abacus calculation methods with modern pedagogical approaches, we turn math from a source of anxiety into an interactive, confidence-building game.

ሜንታል አባከስ አካዳሚ የተመሰረተው በአንድ የጠራ ራዕይ ነው፦ በእያንዳንዱ ኢትዮጵያዊ ልጅ ውስጥ ያለውን የተደበቀ የእውቀት አቅም ማውጣት። ጊዜ የተፈተነውን የአባከስ ስሌት ዘዴ ከዘመናዊ የማስተማር ስልቶች ጋር በማጣመር፣ ሂሳብን ከጭንቀት ምንጭነት ወደ በራስ መተማመን መገንቢያ ጨዋታ እንለውጣለን።

Whether preparing students for Grade 6 or Grade 8 regional exams or starting early with KG 3 learners, our bilingual English/Amharic curriculum ensures that language is never a barrier to deep analytical understanding.

ተማሪዎችን ለክፍል 6 ወይም 8 ክልላዊ ፈተናዎች ማዘጋጀት ወይም ከኬጂ 3 ጀምሮ በጊዜ ማሰልጠን፣ የእኛ እንግሊዝኛ እና አማርኛ ባለሁለት ቋንቋ ስርአተ ትምህርት ቋንቋ ለጥልቅ ትንታኔ ግንዛቤ ፈጽሞ እንቅፋት እንዳይሆን ያደርጋል።

Our Mission
ተልዕኳችን
To empower children with lifelong focus, calculation speed, and problem-solving resilience.
ልጆችን የህይወት ዘመን ትኩረትን፣ የስሌት ፍጥነትን እና ችግሮችን የመፍታት ፅናትን ማስታጠቅ።
Our Approach
አካሄዳችን
Bilingual instruction, custom textbooks, and hands-on drills that engage both hemispheres of the brain.
ባለሁለት ቋንቋ ትምህርት፣ የራስ መማሪያ መጽሐፍት እና ሁለቱንም የአዕምሮ ክፍሎች የሚያሳትፉ ተግባራዊ ልምምዶች።
Classroom Activity
Our Team
የአሰልጣኞች ቡድን

Meet Our Certified Instructors

የተመሰከረላቸው አሰልጣኞቻችንን ያግኙ

Our classes are led by certified educators specializing in developmental mental mathematics and exam tutoring.

ክፍሎቻችን የሚመሩት በልጆች የአዕምሮ ሂሳብ እና በፈተና ዝግጅት ስልጠና ልዩ ባለሙያ በሆኑ የተመሰከረላቸው መምህራን ነው።

Dawit Melaku
Dawit Melaku
አቶ ዳዊት መላኩ
Founder & Lead Instructor
መስራች እና ዋና አሰልጣኝ

Founder of Mental Abacus Academy and author of "የሒሳብን በጣቴ". Offers over 6 years of math teaching and 4 years of abacus expertise, teaching students globally across 11+ countries.

የአካዳሚው መስራች እና የ"የሒሳብን በጣቴ" መጽሐፍ ደራሲ። ከ6 ዓመት በላይ የመምህርነት እና ከ4 ዓመት በላይ የአባከስ ስልጠና ልምድ ያላቸው ሲሆን ከ11 በላይ ሀገራት ላሉ ተማሪዎች ኦንላይን ያስተምራሉ።

Melesse Misganaw
Melesse Misganaw
አቶ መለሰ ምስጋናው
Senior Exam Tutor
ከፍተኛ የፈተና አስተማሪ

Holds an MBA and degrees in Engineering and Math with 18 years of expertise in education and project coordination. Specializes in Grade 6 & 8 national exam prep.

በንግድ ስራ አስተዳደር (MBA) እና ኢንጂነሪንግ የተመረቁ፣ የ18 ዓመታት የትምህርት እና የልማት ድርጅቶች ልምድ ያላቸው። ለክፍል 6 እና 8 ሀገር አቀፍ ፈተና ዝግጅት በከፍተኛ ብቃት የሚያስተምሩ።

Abel Yohannes
Abel Yohannes
አቤል ዩሐንስ
Math Instructor & Private Tutor
የሒሳብ አስተማሪ እና ግል አስጠኝ

Math teacher at Wisdom General Secondary School for over 5 years, also working as a private tutor.

በዊዝደም አጠቃላይ ፩ኛ ደረጃ ት/ቤት ከ5 ዓመት በላይ የሒሳብ መምህር እና በግል አስጠኝ በመሆን የሰራ።

Have questions about our teaching methods?

ስለ ማስተማሪያ ዘዴዎቻችን ጥያቄዎች አሉዎት?